News

22-09-2021

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በርካታ የመንገድና ህንጻ ግንባታዎችን ገንብቶ አጠናቋል፤ እየገነባም ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ከገነባቸው እና እየገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የአብዛኛዎቹን የማማከር ስራ የሰራው ደግሞ የአብክመ መንገድና ህንጻ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት ነው፡፡ እኛም የአብክመ መንገድና ህንጻ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት የማማከር ስራ በሰራባቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ያሳየውን የመፈጸም…
22-09-2021

ኢትዮጵያን ማፍረስ በተለይም አማራን ማጥፋት ካልቻለም ማዳከም ዋና ዓላማ አድርጎ እየተውተረተረ የሚገኘው ትህነግ በአማራ እና አፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ሰላም የመንሳትና የማሸበር እኩይ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ትህነግ ለሶስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፋትና በአለም አደባባይም አንገቷን ሲያስደፋት ቆይቶ በመላ ኢትዮጵያውያን ትግል ከማዕከላዊ መንግስት ቢገለልም እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ በሚል ሰይጣናዊ እሳቤው የኢትዮጵያውያንን ልማትና…
22-09-2021
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ለህልውና ማስከበር ዘመቻው ሙሉ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ፡፡

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ-አውጪ ግንባር) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ሳይታሰብ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የህዝብ ደህንነትንና የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ በማዕከላዊ መንግስት እና በክልላችን መንግስት የህግ ማስከበር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጅ መንግስት…
22-09-2021

በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው ነባሩ የባህር ዳር ከተማ መነሀሪያ አስፓልት ኮንክሪት ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን በፕሮጀክቱ ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ችለናል፡፡ በድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የባህር ዳር ከተማ ነባሩ መነሀሪያ አንዱ ሲሆን ግንባታው የተጎዳውን ነባሩን አስፓልት አንስቶ ደረጃውን በማሳደግ እና ጥራቱን በመጠበቅ የሚገነባ አስፓልት ኮንክሪት የማልበስ ስራ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በኪሎ…
22-09-2021
የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ።
ብር 591,816,447.09 በሆነ ዋጋ በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ። በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በስሩ በከተማው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎችን የሚያገናኙ መንገዶችን ያካተተ ሲሆን በድምሩ 7.84 ኪሎ ሜትር…