News

22-09-2021

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ ሰኔ 03 2012 ዓ.ም የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። በየአመቱ 5 ቢሊዮን በአጠቃላይ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ፕሮጀክት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ባለፈው ዓመት ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በዚህ ዓመትም 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ ግንቦት 28 2012 ዓ.ም ተጀምሯል።…
01-03-2020
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የኮሬ አዲስ አለም አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክትን ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ተፈራረመ።

ድርጅቱ ከኮሬ አዲስ አለም የሚደርሰውን 10.74 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ተፈራርሟል። የፊርማ ስነ ስርዓቱ ዛሬ የካቲት 12 2012 ዓ.ም ሲከናወን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅኔር ሀብታሙ ተገኘ፣ ምክትል ዳይሬክተሮች አቶ ሲሳይ በቀለ…
01-03-2020
የድርጅታችን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ማኔጅመንት አባላት ድርጅታችን እየገነባቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የቦርድ አባላት፣ የአማራ ክልል ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት የዳንግላ ጃዊ የጠጠር መንገድ ሥራ እና የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡ በጉብኝቱ ድርጅታችን…
የውይይት ኘሮግራሙ የጀመረው የዳንግላ ጃዊ የጠጠር መንገድ ሥራ ኘሮጀክትን በመጎብኘት ነበር፡፡ የውይይቱ ተሣታፊዎች የጉብኝት ኘሮግራሙን አጠናቀው እንደተመለሱ የኘላንና ቢዝነስ ደቨሎኘመንት ደጋፊ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አያልነህ ገሰሰ የድርጅቱን የ6 ዓመት የእድገት ጉዞን አቅርበዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አየሁ የዳንግላ ጃዊ የጠጠር መንገድ ጉብኝት እና የድርጅቱን የዕድገት ጉዞ መነሻ በማድረግ ድርጅቱ በተቋቋመ…
02-03-2020
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ካይዘንን እየተገበሩ ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች በመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ትግበራ ምዘና 1ኛ በመውጣት በኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በኩል የእውቅና ሽልማት አገኘ።

የእውቅና ሽልማቱ ድርጅቱ የሁለተኛ ደረጃ ካይዘን ትግበራን በተሻለ የመስራት ፍላጎት በመፈፀም ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳው ታምኖበታል።