የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ።

ደ
የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ።
ብር 591,816,447.09 በሆነ ዋጋ በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ። በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በስሩ በከተማው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎችን የሚያገናኙ መንገዶችን ያካተተ ሲሆን በድምሩ 7.84 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና በተለያዩ ቦታዎች ከ10-30 ሜትር ስፋት ያላቸው ናቸው።
በስምንት የተለያዩ ቦታዎች እየተገነቡ ከሚገኙት መንገዶች መካከል 950 ሜትር ርዝመት ያለው ከመናፈሻ ተቋም የሚደርሰው ባለሁለት አካፋይ መንገድ የስትራክቸር፣ ሰብ ቤዝ ኮሬክሽንና ቤዝ ኮርስ የማልበስ ስራዎች ተጠናቀው አስፓልት ማልበስ ተጀምሯል። የወሰን ማስከበር ችግር በሌለባቸው ሌሎች የመንገዱ ክፍሎችም የቆረጣና ሙሊት፣ የስትራክቸርና ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ፕሮጀክቱን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።