News

22-09-2021

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን እድገትና የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ የቻለ የክልላችን ተቋም ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መጋቢያው ጣሰው ተናገሩ። የክልሉን የመሰረተ ልማት ተደራሽነት እና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ አስፈላጊነታቸው ታምኖበት ከተቋቋሙት የመንግስት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት…
22-09-2021

የምዕራብ ጎጃሟን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ከአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ጋር የሚያገናኘው የላሊበላ አሹዳ ዝህብስት ፈንድቃ መንገድ ስራ ፕሮጀክት 98 ከመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለፀ። ይህ መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 67 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 7 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ትልልቅ ድልድዮች፣ ስትራክቸር፣ ቱቦ ከልቨርት፣ ስላቭ ከልቨርት እና ሌሎች ስራዎችን የያዘ ነው። መንገዱ በተለይ 60 ሜትር ርዝመት ያለውን ግዙፉን የበለስ ወንዝ ድልድይ እንዲሁም 22 ሜትር ርዝመት…
22-09-2021

የደንበጫ የፈረስ ቤት 69.8 ኪሎ ሜትር አስፓልት ኮንክሬት መንገድ ስራ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ሃምሌ 3/2012 ዓ.ም ውል የተፈራረመው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከደጋ ዳሞት ወረዳ አስተዳደር የጋራ የትውውቅ እና የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
የጋራ የውይይት መድረኩን የደጋ ዳሞት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋለ እንዳለ እና የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው ዓለማየሁ በጋራ በመሆን በዳቦ…
22-09-2021
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በቡሬ ከተማ ከትንሳኤ ሆቴል እስከ ኢትዮ ቴሌኮም የሚደርስ የ1.52 ኪሎ ሜትር አስፓልት ኮንክሪት መንገድ በ45,639,948.48 ብር ገንብቷል። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጌትነት አጥናፉ እንዳሉት ቀደም ብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ አስፓልት መንገድ ቢሰራም ጥራቱን የጠበቀ ስላልነበር ሊፈርስና ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠር ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን አመኔታ ቀንሶ ቆይቷል። አሁን ግን ይላሉ አቶ…
22-09-2021

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አለት ሰንጥቆ ጥራት ያለው መንገድ የመገንባት አቅም ያለው ድርጅት ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ወዳጀ ተናገሩ። የዳንግላ ጃዊ፣ ላሊበላ አሹዳ ዝህብስት ፈንድቃና አርብ ገበያ ጋግቢያ ኩርባ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የድርጅቱን አቅም ማሳያ ፕሮጀክቶች ናቸው ያሉት አቶ ደሳለኝ በተለይም አስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥና ከፍተኛ የሆነ አለት ባለው የዳንግላ ጃዊ መንገድ ስራ ፕሮጀክት…