የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ለህልውና ማስከበር ዘመቻው ሙሉ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ፡፡

ቨ
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ለህልውና ማስከበር ዘመቻው ሙሉ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ፡፡

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ-አውጪ ግንባር) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ሳይታሰብ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የህዝብ ደህንነትንና የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ በማዕከላዊ መንግስት እና በክልላችን መንግስት የህግ ማስከበር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጅ መንግስት የትግራይ ህዝብ በተራዘመ ጦርነትና በረሀብ እንዳይጎዳ እንዲሁም የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ መንግስት በግሉ የተናጠል ተኩስ አቁም ቢያደርግም ሀገር ሰላም ከሆነ ነገ በወንጀል እጠየቃለሁ ብሎ የፈራውና ራሱን በህዝብ ጉያ ስር መደበቅ የፈለገው ዘራፊው የትህነግ ትራፊ ቡድን በተለይ የአማራ ክልልን ህዝብ በዋና ጠላትነት ፈርጆ ጥቃት ለመሰንዘር ራሱን ከማደራጀትና የጦርነት ነጋሪት ከመጎሰም አልፎ በክልላችንና በሌሎች አጎራባች ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ወረራና ጥቃት ፈጽሟል፡፡
የአሸባሪውን ቡድን ወረራ ለመመከትም መላ የሀገራችን ህዝብ በታላቅ ሀገራዊ የአንድነት ስሜት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት በበኩሉ የህልውና ማስከበር የክተት አዋጅ አውጇል፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
የክልላችን መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል በዋና ቢሮና በፕሮጀክቶች የሚሰሩ ሁሉም የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮችና ሰራተኞች ሙሉ የአንድ ወር ደመወዛቸውን (100%) ለህልውና ማስከበር ዘመቻ ለመስጠት ወስነዋል፡፡