News

30-10-2025
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የአደረጃጀት፣ የስያሜ እና የሎጎ ለውጥ ይፋዊ የማስተዋወቂያ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የኮርፖሬሽኑ መሪዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የቀድሞው የአማራ…
30-10-2025
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የላቀ ለውጥ እና ሁለንተናዊ ከፍታ ላይ ለመድረስ የሚያስችለውን የአደረጃጀት፣ የስያሜ እና የሎጎ ለውጥ ማድረጉ የካቲት 13/ 2017 ዓ.ም በተካሄደው የማስተዋወቅ እና ስራ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተገልጿል። በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽኑ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የጠጠር እና የአስፓልት መንገድ፣ ድልድዮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ሌሎች ግንባታዎችን መሥራቱን ተናግረዋል…
30-10-2025
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ወደ ኮርፖሬሽንነት ደረጃ ማደጉን ተከትሎ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችለውን አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት አጸደቀ።

ድርጅቱ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ ማደጉን ተከትሎ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችል አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት መፅደቁን ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና…
30-10-2025
«አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለሌሎች ድርጅቶች ምሳሌ መሆን እንደሚቻል ያስተማረ ድርጅት ነው !» ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የአመሥድ ቦርድ ሰብሳቢ

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለሌሎች ድርጅቶች ምሳሌ መሆን እንደሚቻል ያስተማረ ድርጅት ነው ሲሉ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የአመሥድ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ ገልጸዋል። ድርጅቱ በአንድ ወቅት አፈጻጸሙ ቀንሶ የነበረ ቢሆንም…
30-10-2025
ክቡር ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጎበኙ።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በባህር ዳር ከተማ እየገነባው በሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ምሽት ላይ ተገኝተው ተዘዋውረው በመመልከት ሰራተኞችን አበረታተዋል። በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ…