News

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲቲዩት በመጡ አሰልጣኞች ከመስከረም 7-14/2011 ዓ.ም ከ130 በላይ ለሚሆኑ የድርጅቱ አመራሮች፣ የምህንድስና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጭ ሙያተኞች በኘሮጀክት ማኔጅመንት (Construction Procurement and Building Process, Contract Administration, Construction claim Management, Project Planning, Scheduling,…
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የሔራን የበጎ አድራጐት ማህበር ለሚንከባከባቸው 37 ህፃናትና ወጣቶች 106, 798 ብር ወጭ በማድረግ የትምህርት ቁሣቁስ (ቦርሣ፣ የጽሀፈት መሣሪያ፣ አልባሣት፣ጫማ) ና 18.5 ኩንታል የፊኖ ዶቄት በአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከዳንግላ ጃዊ መንገድ ስራ ፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት ጋር በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ዙሪያ ህዳር 8 2011 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ ውጤታማ የምክክር መድረክ አካሄደ።

በውይይቱ የተሳተፉ የመንገዱ ተጠቃሚዎች ድርጅቱ እያካሄደ ያለውን የመንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ በአካል በመገኘት እየተከናወነ ያለውን እስከ 75 ሜትር የሚደርሰውን ከፍተኛ የጋራ ቆረጣ ስራ እና የፍንዳታ ስራ በመመልከት አድናቆታቸውን የገለፁ ሲሆን ግንባታውም…
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለ 235 የድርጅቱ ሰራተኞች ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 3 2011 ዓ.ም በሁለት ዙር በዳንግላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ካይዘን ስልጠና ሰጠ። ድርጅቱ ስልጠናውን የሰጠው የመጀመርያ ደረጃ ካይዘን ስልጠና ላልወሰዱ ሰራተኞች ነው። ድርጅቱ በ 2010 በጀት ዓመት የካይዘንን መርህ በመከተልና በመተግበር አበረታች ለውጦችን አስመዝግቧል። በተለይም የሀብት ብክነትን በመከላከል ረገድ ድርጅቱ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።