ዜናዎች

28-02-2022
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የ2014 በጀት ዓመት የፕሮጀክቶች የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

በግምገማው የሁሉም ኘሮጀክቶች የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በኮንስትራክሽን ዋና የሥራ ሂደት በኩል ቀርቦ ግምገማ አዘል ውይይት ተደርጐበታል፡፡
በመድረኩም የድርጅቱ ኮር አመራር፣ የማኔጅመንት አባላት የኘሮጀክት ኃላፊዎች እና ኦፊሰ መሃንዲሶች፣ የዋናው ቢሮ የኮንስትራክሽንና ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
28-02-2022
በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደብረ ማርያም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ 85 ከመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የደብረ ማርያም መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ማስተማር ስራ እንቅፋት የሚሆን ዘርፈ ብዙ ችግር ካለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው። ትምህርት ቤቱ በክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር የሚገኝ ይሁን እንጅ አንድ ትምህርት ቤት ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን በበቂ ሁኔታ የተሟሉለት…
16-02-2022
የቡሬ እና የ4ቱን የገጠር የሽግግር ማዕከላት አስፓልት ግንባታ ኘሮጀክቶች ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ውይይት ተካሄደ፡፡

የቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪካል ሥራዎችን እና የ4ቱን የገጠር ሽግግር ማዕከላት / እንጅባራ፣ ፍ/ሰላም፣ ዳንግላ፣መራዊ/ አስፓልት ግንባታ ኘሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ውይይት የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የኮር እና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኘሮጀክቶቹ ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ የካቲት 9/2014…
16-02-2022
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች 69.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የደንበጫ ፈረስ ቤት ሰቀላ አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው ዓለማየሁን ጨምሮ ሌሎች የኮር አመራር አባላት ተገኝተው እስካሁን በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ተግባራትን ከጎበኙ በኌላ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም አሁን ካለበት በተሻለ ለማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፕሮጀክቱ ሰራተኞች ጋር ገምቢ…
16-02-2022
የጎንጅ ቆለላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ የሶስተኛ ወገን ችግር ከተፈታለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የኘሮጀክት ኃላፊው አስታወቁ፡፡

የኘሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተስፋየ ይህንን የገለጹት የመንገድ ግንባታው ያለበትን ደረጃ የመሥክ ምልከታ ላደረገው የድርጅቱ አመራር ነው፡፡
የጎንጅ ቆለላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ አጠቃላይ ርዝመቱ 10.7 ኪ/ሜ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በ2013 በጀት ዓመት በጥቂት ወራት ጊዜ ውስጥ…