የቡሬ እና የ4ቱን የገጠር የሽግግር ማዕከላት አስፓልት ግንባታ ኘሮጀክቶች ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ውይይት ተካሄደ፡፡

rtc
የቡሬ እና የ4ቱን የገጠር የሽግግር ማዕከላት አስፓልት ግንባታ ኘሮጀክቶች ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ውይይት ተካሄደ፡፡

የቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪካል ሥራዎችን እና የ4ቱን የገጠር ሽግግር ማዕከላት / እንጅባራ፣ ፍ/ሰላም፣ ዳንግላ፣መራዊ/ አስፓልት ግንባታ ኘሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ውይይት የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የኮር እና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኘሮጀክቶቹ ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ የካቲት 9/2014 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም በኘሮጀክቶቹ ያለው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ የተገመገመ ሲሆን ኘሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ እንቅፋት የፈጠሩ ችግሮችም አንድ በአንድ ተነስተው ውይይት ከተካሄደ በኋላ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
እነዚህን ኘሮጀክቶች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የግብዓት አቅርቦቱን የተሳለጠ ለማድረግ በዋናው ቢሮ በኩል እንደሚሠራ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን የኘሮጀክቶቹ አመራሮችና ሰራተኞችም ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ኘሮጀክቶቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ መሥራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡