የጎንጅ ቆለላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ የሶስተኛ ወገን ችግር ከተፈታለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የኘሮጀክት ኃላፊው አስታወቁ፡፡
የኘሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተስፋየ ይህንን የገለጹት የመንገድ ግንባታው ያለበትን ደረጃ የመሥክ ምልከታ ላደረገው የድርጅቱ አመራር ነው፡፡
የጎንጅ ቆለላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ አጠቃላይ ርዝመቱ 10.7 ኪ/ሜ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በ2013 በጀት ዓመት በጥቂት ወራት ጊዜ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ችግር የሌለበትን 5.96 ኪ/ሜ ደረጃውን የጠበቀ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ እንደተገነባ እና የዲች ግንባታ ሥራም እንደተጀመረ ከኘሮጀክት ኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡
የኘሮጀክቱ ኃላፊ አያይዘውም ለዲች ከቨር ከሚያስፈልግ 8,500 ኘሪካስት ውስጥ 7,600 እንደተመረተ ቀሪውንም ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ እና ከዚህ ጎን ለጎንም ለአስፓልት መንገድ የሚያገለግል የከርቭስቶን ምርት ለመጀመር የናሙና ምርቶች ተመርተው የጥራት ደረጃ ፍተሻውን እንዳሟላ አብራርተዋል፡፡
የሶስተኛ ወገን ችግር ለመፍታት በተደረገው ጥረት በአሁኑ ሰዓት 1 ኪ/ሜ የሚሆን ቦታ ነፃ የተደረገ እና ለግንባታ የተመቻቸ ሲሆን ይህንን ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአስፓልት ኮንክሪት የማልበስ ሥራውን እንደሚያጠናቅቁ እና የዲች ግንባታ ሥራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
የኘሮጀክት ኃላፊው ለሥራቸው መሣካት ያስፈልጋሉ ያሏቸውን የግንባታ ግብአቶች በድርጅቱ እንዲሟሉላቸው እና የሶስተኛ ወገን ችግሩ ያልተፈታለት ቀሪ የመንገዱን አካል በቀጣይም ሥራቸውን እንዳያዘገየው ትኩረት እንዲሠጠው አሣስበዋል፡፡
በመስክ ምልከታና ድጋፍ ለማድረግ በኘሮጀክቱ የተገኘው የድርጅቱ አመራርም የመንገድ ግንባታው ያለበትን ደረጃ ከተመለከተ በኋላ የኘሮጀክቱን ሠራተኞች ሥራውን በአጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮችና ሁሉን አቀፍ በሆኑ ሃሣቦች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱም ወቅት ሠራተኞቹ ለኘሮጀክቱ እና ለድርጅቱ ተግባራት መሣካት ይጠቅማሉ ያሏቸውን ሀሣቦች አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም የድርጅቱ አመራር የመንገድ ግንባታ ሥራው በአጠረ ጊዜ ከብክነት በፀዳ መልኩ እንዲጠናቀቅ እንዲሁም የተጠየቁት መሠረታዊ የግንባታ ግብአቶች መሟላት እንዲችሉ አሥፈላጊው ሁሉ ጥረት እንደሚደረግ እና በሠራተኛው በኩል ለተነሱ ሀሣቦችም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡