ዜናዎች

30-04-2024
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የድርጅታችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት እና ሁሉም የዋና ቢሮ ሰራተኞች በተገኙበት ዛሬ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ የበጀት ዓመቱ የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕላንና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ደጋፊ ስራ ሂደት…
14-02-2024
የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ገለጹ፡፡

የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ አባይነህ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡ በባህር ዳር ከተማ በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 8.5 ኪ.ሜ ርዝመት እና 40 ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ የሆነ…
14-02-2024
''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ለድርጅታችን የዋና ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግሥት ሠራተኛው ሚና በሚሉ ሁለት ዓበይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከየካቲት 04-05/ 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል። በስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ…
10-02-2024
ድርጅታችን የተከዜ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታን በይፋ ጀመረ።

ድርጅታችን የተከዜ ድልድይ የሰብ ስትራክቸር ስራዎችን ብር 256,140,691.61 በሆነ በጀት ለመገንባት ስምምነት ፈጽሞ ግንባታውን በይፋ ጀምሯል። ከሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው የተከዜ ድልድይ በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የዝቋላ እና ሰሀላ-ሰየምት ወረዳዎች መካከል የሚገኝ ሲሆን ብሔረሰብ ዞኑን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጋር በሚያገናኘው ዋና…
30-12-2023
ያለፈውን በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም በያዝነው በጀት ዓመትም ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን የድርጅታችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ ገለጹ፡፡

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በአሁኑ ሰዓት ድርጅታችን ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በተመለከተ ለብዙሐን መገናኛ ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የድርጅታችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ በ2015 በጀት ዓመት የተመዘገበውን የላቀ አፈጻጸም…