ዜናዎች

22-09-2021
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለዋና ቢሮ እና ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት አባላት የ2012 እቅድ አፈጻጸምን መነሻ ያደረገ ግምገማ አዘል ስልጠና ከመስከረም 19 እስከ 23 2013 ዓ.ም ሰጥቷል።
ግምገማው በድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አለማየሁ የተመራ ሲሆን በሎጅስቲክስ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባይሌ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማው እንዲሁም በዋናው ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር…
22-09-2021

ለድርጅታችን የገልባጭ መኪና፣ የውሀ ቦቲ፣ ኬሬር ትራክ እና ሎቤድ ኦፕሬተሮች በጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬ መስከረም 05 2013 ዓ.ም እየተሰጠ ነው። ስልጠናው እየተሰጠ ያለው በድርጅታችን ሎጅስቲክስ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባይሌ እና የመሳሪያዎች አስተዳደርና ጥገና ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ ጌታቸው ደስየ ሲሆን ከጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ…
22-09-2021

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን እድገትና የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ የቻለ የክልላችን ተቋም ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መጋቢያው ጣሰው ተናገሩ። የክልሉን የመሰረተ ልማት ተደራሽነት እና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ አስፈላጊነታቸው ታምኖበት ከተቋቋሙት የመንግስት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት…
22-09-2021
የምዕራብ ጎጃሟን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ከአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ጋር የሚያገናኘው የላሊበላ አሹዳ ዝህብስት ፈንድቃ መንገድ ስራ ፕሮጀክት 98 ከመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለፀ። ይህ መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 67 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 7 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ትልልቅ ድልድዮች፣ ስትራክቸር፣ ቱቦ ከልቨርት፣ ስላቭ ከልቨርት እና ሌሎች ስራዎችን የያዘ ነው። መንገዱ በተለይ 60 ሜትር ርዝመት ያለውን ግዙፉን የበለስ ወንዝ ድልድይ እንዲሁም 22 ሜትር ርዝመት ያለውን…
22-09-2021
የደንበጫ የፈረስ ቤት 69.8 ኪሎ ሜትር አስፓልት ኮንክሬት መንገድ ስራ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ሃምሌ 3/2012 ዓ.ም ውል የተፈራረመው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከደጋ ዳሞት ወረዳ አስተዳደር የጋራ የትውውቅ እና የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
የጋራ የውይይት መድረኩን የደጋ ዳሞት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋለ እንዳለ እና የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው ዓለማየሁ በጋራ በመሆን በዳቦ ቆረሳ ስነ…