ድርጅታችን የተከዜ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታን በይፋ ጀመረ።
ድርጅታችን የተከዜ ድልድይ የሰብ ስትራክቸር ስራዎችን ብር 256,140,691.61 በሆነ በጀት ለመገንባት ስምምነት ፈጽሞ ግንባታውን በይፋ ጀምሯል። ከሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው የተከዜ ድልድይ በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የዝቋላ እና ሰሀላ-ሰየምት ወረዳዎች መካከል የሚገኝ ሲሆን ብሔረሰብ ዞኑን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጋር በሚያገናኘው ዋና መንገድ ላይ የሚያገኛኝ ነው።
ከዚህ ቀደም በ1998 ዓ.ም ተገንብቶ የነበረው ድልድይ በ2012 ዓ.ም በመሰበሩና በደለል በመዋጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዓመታት በከፍተኛ ችግር ውስጥ መቆየታቸው የተገለጸ ሲሆን ድርጅታችን የአዲሱን ድልድይ የሰብ ስትራክቸር ስራ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ኃላፊነት ወስዶ ስራውን ጀምሯል። በአጠቃላይ ድርጅታችን የሰብ ስትራክቸር ስራዎችን ማለትም የውሀ አቅጣጫ ማስቀየሻ ግድብ፣ የደለል ማስወገድ፣ የዋናውን ድልድይ መሰረትና ምሰሶ እንዲሁም ምሰሶዎችን የሚያገናኝ (ፒር ካፕ) እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን በሶስት ወራት ጊዜ ገንብቶ ለማጠናቀቅ አቅዶ ወደ ስራ ገብቷል።