እንደ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ያለ ተቋራጭ ማግኘት እድለኝነት ነው ሲሉ የአሊቾ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ገለጹ፡፡
እንደ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ያለ ተቋራጭ ማግኘት እድለኝነት ነው ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የአሊቾ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ገለጹ፡፡ ኃላፊው ይህን ያሉት የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አፈጻጸምን በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ባደረግንላቸው ወቅት ነው፡፡ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክትን እየገነባ የሚገኝ ሲሆን የፕሮጀክቱን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉን የአሊቾ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድን አነጋግረናቸዋል፡፡
እንደ ጽ/ቤት ኃላፊው ገለጻ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለው አፈጻጸም በጣም ተስፋ ሰጭ እና ህብረተሰቡንም ያስደሰተ ነው፡፡ የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ግንባታ ከተጀመረ ረጅም ዓመት ያስቆጠረና የመልካም አስተዳደር ችግርም ፈጥሮ ቆይቶ ነበር ያሉት ጽ/ቤት ኃላፊው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ፕሮጀክቱን ከተረከበ በኋላ ግን አበረታች የስራ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ህብረተሰቡም አሁን ባለው የስራ እንቅስቃሴ ደስተኛ በመሆኑ ለረጅም አመታት ካሳ ሳይከፈለው ቢቆይም የመንገዱ ግንባታ እንዳይስተጓጎል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ሲሉ አቶ መሀመድ አህመድ ጨምረው አብራርተዋል፡፡
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ወደ ወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ከገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ መሀመድ አህመድ እንደዚህ ያለ ሀገር በቀል ተቋራጭ ማግኘት እድለኝነት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም እንደ ባለድርሻ አካል ለፕሮጀክቱ በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቅ ኮንትራክተሩን የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግ እያገዝን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ድርጅታችን የሚያከናውናቸውን ተግባራት፣ የጨረታ እና የቅጥር ማስታወቂያዎችን ለማግኘት የድርጅታችንን፡-
ፌስ ቡክ፡ www.facebook.com/AmharaRoadWorksEnterprise
ድረ ገጽ፡ www.arwe.et
ቴሌግራም፡ www.t.me/AmharaRoadWorksEnterprise
ዩቲዩብ፡ www.youtube.com/AmharaRoadWorksEnterprise ይጎብኙ፡፡