የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ገለጹ፡፡

marda
የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ገለጹ፡፡

የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ አባይነህ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡ በባህር ዳር ከተማ በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 8.5 ኪ.ሜ ርዝመት እና 40 ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ የሆነ የመኪና፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድን እንዲሁም አረንጓዴ ቦታ ግንባታን ያካተተ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከሶስተኛ ወገን ችግር ነጻ በሆነው የመንገዱ ክፍል የቆረጣና ሙሊት ስራዎች ሲሆን አፈጻጸሙም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ አባይነህ ደሰለኝ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም 40 ሜትር ስፋት፣ 8.5 ሜትር ቁመት እና 4 ሜትር ስፋት ያለውን ከልቨርት ጨምሮ የውሀ ማፋሰሻ እና ሌሎች የስትራክቸር ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በማህበር ለተደራጁ በርካታ ወጣቶች በፕሮጀክቱ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የዲች ግንባታ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል አሁንም ድረስ ያልፈቱ የሶስተኛ ወገን ችግሮች (የመብራት ፖሎች፣ የውሀ መስመሮች፣ አጥር እና ቤቶች) መኖራቸው በሁሉም የፕሮጀክቱ ክፍል ወጥ በሆነ መልኩ ሁሉንም ተግባራት ለመጀመርና ለመስራት አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረባቸው እንደሆነ የገለጹት ፕሮጀክት ኃላፊው እነዚህ ችግሮች በቶሎ መፍትሄ እንዲያገኙ ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
marda