የዋርካው- ምድረገነት- ዘንዘልማ እና የቅ/ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገለጹ፡፡

የዋርካው- ምድረገነት- ዘንዘልማ እና የቅ/ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገለጹ፡፡

ድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ አጼ ቴወድሮስ ክፍለ-ከተማ እየገነባቸው የሚገኙት የዋርካው- ምድረገነት- ዘንዘልማ እና የቅ/ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረ-ገነት ታክሲ ማዞሪያ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገለጹ፡፡ እንደ ፕሮጀክት ኃላፊው ገለጻ 3.2 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የዋርካው- ምድረገነት- ዘንዘልማ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት 6 ሳ.ሜ ውፍረት ያለው የመጀመሪያ ሌየር አስፓልት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ ሁለተኛውን እና የመጨረሻውን ሌየር አስፓልት የመደረብ ስራን ጨምሮ በመሰራት ላይ ያሉ የኤሌክትሪክ እና የእግረኛ መንገድ ስራዎችን ጨምሮ ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ እየተሰራ መሆኑን ፕሮጀክት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የቅ/ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረ-ገነት ታክሲ ማዞሪያ አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሮጀክት ኃላፊው ከአዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ ያለው የመጀመሪያ ዙር አስፓልት ስራ ሙሉ በሙሉ እንደተጠናቀቀና ሁለተኛውን ሌየር የመደረብ ስራም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡ በአንጻሩ ከቅ/ገብርኤል እስከ አዲሱ አስፓልት ያለው በሶስተኛ ወገን ችግር ምክንያት ግንባታው የዘገየ መሆኑን ገልጸው አሁን ግን የሶስተኛ ወገን ችግር ስለተፈታ ግንባታውን በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ፕሮጀክት ኃላፊው አቶ ተስፋለም አድባሩ ገልጸዋል፡፡

ድርጅታችን የሚያከናውናቸውን ተግባራት፣ የጨረታ እና የቅጥር ማስታወቂያዎችን ለመከታተል፡-
ፌስ ቡክ፡ www.facebook.com/AmharaRoadWorksEnterprise
ቴሌግራም፡ www.t.me/AmharaRoadWorksEnterprise
ዩቲዩብ፡ www.youtube.com/AmharaRoadWorksEnterprise ይጎብኙ፡፡
warkaw