የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ችግኝ ተከሉ።

ችግኝ ተከላ

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ ሰኔ 03 2012 ዓ.ም የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። በየአመቱ 5 ቢሊዮን በአጠቃላይ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ፕሮጀክት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ባለፈው ዓመት ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በዚህ ዓመትም 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ ግንቦት 28 2012 ዓ.ም ተጀምሯል።
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞችም በዛሬው እለት ሀገር በቀል ችግኞችን በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመትከል የአረንጓዴ መርሀ ግብሩ ተሳታፊ ሆነዋል። በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች ሙሉ በሙሉ እንዲፀድቁ ዘላቂ የሆነ እንክብካቤ የማድረግ ስራ የሚሰራ ይሆናል።
.
.
.
 ችግኞችን በመትከል የአፈር መሸርሸርን ብሎም የአየር ንብረት መዛባትን እንከላከል !!
 የህዳሴ ግድባችን እናት የሆነውን የጣና ሀይቅን ከእንቦጭ አረም እንጠብቅ !!
 አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ከኮሮና በሽታ እንጠብቅ !!