የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለ 235 የድርጅቱ ሰራተኞች ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 3 2011 ዓ.ም በሁለት ዙር በዳንግላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ካይዘን ስልጠና ሰጠ። ድርጅቱ ስልጠናውን የሰጠው የመጀመርያ ደረጃ ካይዘን ስልጠና ላልወሰዱ ሰራተኞች ነው። ድርጅቱ በ 2010 በጀት ዓመት የካይዘንን መርህ በመከተልና በመተግበር አበረታች ለውጦችን አስመዝግቧል። በተለይም የሀብት ብክነትን በመከላከል ረገድ ድርጅቱ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።