የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የአሊቾ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከድር ገለጹ፡፡
ዋና አስተዳዳሪው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በመጀመሪያ ወደ ፕሮጀክቱ እንደገባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረውን መንገድ የመጠገን እና የትራፊክ ፍሰቱ እንዳይስተጓጎል የማድረግ ስራ በመስራቱ እንደ ወረዳ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን ይህም ተግባር በርግጥም ችግር ለመፍታት የመጣ ድርጅት መሆኑን ያመላክታል ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
ተቋራጩ አሁን ያለው አፈጻጸም የተሻለ ይሁን እንጅ በአፈጻጸሙ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩት ጉዳዮች አንዱ የአካባቢው የአየር ሁኔታ ተለዋዋጭነት መሆኑን ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ደጋማው አካባቢ አብዛኛውን ጊዜ ዝናብ የሚዘንብበት ሁኔታ ስላለ ዝናብ በማይዘንብበት ወቅት ተጨማሪ ማሽንና የሰው ሀይልን በመጠቀም እንዲሁም ተጨማሪ ሰዓት በመስራት ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ካልተደረገ ለፕሮጀክቱ በፍጥነት መጠናቀቅ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ አማን ከድር ህብረተሰቡ የአስፓልት ስራው ተጀምሮ ለማየት ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንጻር ለአስፓልት ዝግጁ የሆነውን አካባቢ አስፓልት የማንጠፍ ስራ ቢጀመር መልካም ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ወረዳው እንደ አንድ ባለድርሻ አካል ለመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ አፈጻጸም እንቅፋት የሚሆን ችግር እንዳይፈጠር የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡