155 ሜትር ርዝማኔ ያለውን የተከዜ ቤሊብሪጅ ግንባታ ተጠናቀቀ ::

tek
155 ሜትር ርዝማኔ ያለውን የተከዜ ቤሊብሪጅ ግንባታ ተጠናቀቀ ::

በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ እና ሰሃላ ሰየምት ወረዳዎች መካከል 155 ሜትር ርዝማኔ ያለውን የተከዜ ቤሊብሪጅ ግንባታን ከኮትራት ጊዜው ቀድሞ መጠናቀቁን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ ተናገሩ። የቤሊ ብሪጅ የሰቭስትራክቸር ሥራዎችን ከኮንትራት ጊዜው ቀድሞ ለማጠናቀቅ አይደፈሬውን የተከዜን ወንዝ ፍሰት አቅጣጫ ማስቀየር ወይንም ማስቆም፣ በደለል የተሞላውን የድልድዩን የግንባታ ቦታ ከደለል ነጻ ማድረግ ፣ የዋና ድልድዩን የመሰረት እና ምሰሶን እንዲሁም ምሰሶዎችን የሚያገኛኘውን የፒርካፕ ሥራዎችን ያለምንም ዕረፍት ሌት ተቀን መስራትን ይጠይቃል።

በክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ቀጥተኛ የሆነ ክትትል የሚደረግበትን ይህንን የተከዜ ድልድይ ግንባታ እውን ማድረግ የድርጅታችን የመፈጸም አቅም አጉልቶ ለማሳየት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን በመገንዘብ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች እና ማኔጅመንቱ ክትትልና ድጋፍ የተቀላጠፈ የግብዓት አቅርቦት እና ፈጣን የውሳኔ አሰጣጥ ጥበብ በእጅጉ ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው።
ይህንን መልካም አጋጣሚ መሬት ለማስነካት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት አስጀምሮ እንዲመጣ በዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ተልዕኮ ቢሰጠውም ግንባታውን አስጀምሮ መምጣት ብቻ ውጤት ሊመጣ እንደማይችል ቅድመ ፕሮጀክት ግምገማ በማድረግ ፕሮጀክቱን አስጀምሮ ከመምጣጥ በላይ በፕሮጀክቱ አስቸጋሪ ነባራዊ ሁኔታ ሳይበገር በከፍተኛ እልህና ጥረት ጠንካራ እና ብስለት የተሞላበትን የአመራር ጥበብን በመጠቀም በፕሮጀክቱ ከአንድ ወር በላይ ውሎ በማደር ሰርቶ በማሰራት የፕሮጀክቱን ከኮንትራቱ ባጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማድረግ በመቻሉ በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እና ማኔጅመንት አባላት በኩል ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል።

ፕሮጀክቱ የኮንትራት ጊዜ አራት ወር የተሰጠው ቢሆንም ፕሮጀክቱ በሶስት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የድርጅቱ ማኔጅመንት የዕለት ከዕለት ክትትልና ድጋፍ በእጅጉ የሚበረታታ እና የተገኘው ልምድ በሚገባ ተቀምሮ ወደ ሌሎች ፕሮጀክቶች ሊሰፋ ይገባል ተብሏል፡፡ የተከዜ የቤሊ ብሪጅ ግንባታን የሚያካሂደው ቡድን የመሪውን የአመራር ጥበብ ፣ትጋት እና እልህን በመላበስ የቀኑ ሃሩር እና ቁር ሳይበግራቸው ያሳዩት ታላቅ የግንባታ ጀግንነት ከድርጅታችንም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ባህልን እና የይቻላል መንፈስን በተግባር ማሳየት ችለዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው በቅድመ ፕሮጀክት እንቅስቃሴው ዝቅተኛ ግምት የነበራቸው የዋግኸምራ እና አካባቢው አመራርና ማህበረሰብም ተከዜን ሲፈልግ የሚገድብ ሲፈልግ የሚለቅ ሃገር በቀል የኮንስትራክሽን ድርጀት ከማግኘታችን በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የድልድይ ግንባታውን ከዚህ ማድረስ በመቻሉ ለድርጅታችን አመራርና ሰራተኞች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል ።

ሌላው የግል የመንገድ ሥራ ተቋራጮች አሁን ባለው ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊገነቧቸው የማይችላቸውን ነገር ግን በጣም አስፈላጊ መዳረሻ መንገዶችን በመስራት ረገድ ያለውን የኮንስትራክሽን ገበያ ክፍተት በመሙላት ህዝቡን የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን እንደ መሆኑ መጠን በ1998 ዓ.ም ተገንብቶ የነበረው ድልድይ በደለል ከመሞላቱ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ መንገዱ ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኘው ለዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ችግር ፈች ሆነን በመገኘታችን ኩራት ይሰማናል፡፡
tek2