የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲቻል የሶስተኛ ወገን ችግሮች እንዲፈቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡

pm
የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲቻል የሶስተኛ ወገን ችግሮች እንዲፈቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በአሁኑ ሰዓት እየገነባቸው ከሚገኙ የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች መካከል የወራቤ ቦጆ በር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ ይህንን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ግንባታ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ድርጅታችን ሙሉ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ ቢገባም በአካባቢው የአየር ሁኔታ እና በሶስተኛ ወገን ችግሮች ምክንያት በታቀደው ልክ ለመስራት አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ጥሩነህ አዱኛ ገልጸዋል፡፡

እንደ ፕሮጀክት ኃላፊው ገለጻ የሶስተኛ ወገን ችግሮችን መፍታት ምንም እንኳን በዋናነት የተቋራጩ ተግባር ባይሆንም ፕሮጀክቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በተቋራጩ በኩል ካለ ከፍተኛ ዝግጁነትና ፍላጎት አንጻር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከርና በመተባበር በመስራት የሶስተኛ ወገን ችግር የነበረባቸውን የተወሰኑ አካባቢዎች ችግር መፍታት እና ስራውን ማስቀጠል ተችሏል፡፡ ይሁን እንጅ እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች ጥሩ ውጤት የተገኘ ቢሆንም የሶስተኛ ወገን ችግሮች ሙሉ በሙሉ የተፈቱ ባለመሆኑ በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው ያሉት ፕሮጀክት ኃላፊው ቀሪ የሶስተኛ ወገን ችግሮችን ለመፍታት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም መንገዱ የሚገነባበት አካባቢ የበልግ ዝናብ የሚያገኝ መሆኑ ለመንገድ ስራ ምቹ አለመሆኑና የመንገዱን ጥራ ለማስጠበቅ ዝናብ የሌለባቸውን ቀናት እየጠበቁ መስራት የግድ ስለሚሆን በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ እንዳለው ከፕሮጀክት ኃላፊው ማብራሪያ ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም የአካባቢው የአየር ሁኔታ እና የሶስተኛ ወገን ችግሮች በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ አስፈላጊ ስትራቴጅዎችን በመቀየስ እየሰሩ እንደሆነ ፕሮጀክት ኃላፊው አቶ ጥሩነህ አዱኛ ገልጸዋል፡፡
wora