የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራርና ሰራተኞች የተቋሙን ፕሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራርና ሰራተኞች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከደንበጫ ፈረስ ቤት እንዲሁም በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከመብራት ኃይል ማርዳ ኤርፖርት እና ዋርካው ዘንዘልማ ምድረገነት እየተገነባ የሚገኘውን አሰፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አማካሪ ኮለኔል አለበል አማረ እና የድርጅቱ ማኔጅመነት አባላትና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ሰራተኞች እንደ ድርጅት አሁን ተቋሙ ያለንበትን ወቅታዊ የመፈጸም እና የማስፈጸም ብቃት እና የፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ በውል ተገንዝቦ በቀጣይ የፕሮጀክቶችን ዉጤታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ ሙያዊ ተግባራትን ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው፡፡
ስራትኞችም በመስክ ጉብኝቱ የፕሮጀክቶችን የሥራ እንቅስቃሴ በአካል ተገኝተው ምልከታ በማድረጋቸው ተደስተዉ እንዲሁም በፕሮጀክት ሰራተኞች ተነሳሽነት እና በእስካሁኑ የስራ ዉጤት ተደንቀዉ ወደ ፊት የድርጅታችንን እና የፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ በማስቀጠል ፕሮጀክቶች ለሚጠይቋቸዉ ጥያቄዎች ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ፈጣን አገልግሎት እና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡