በባህር ዳር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በአባይ ራስ ቀበሌ እየተገነባ ያለዉ ዋርካዉ ምድረገነት ዘንዘልማ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
መንገዱ 3.2 ኪሎሜትር ርዝማኔ እና የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ 30 ሜትር ስፋት ያለዉ ባለመንታ መንገድ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የመንገዱ ግንባታ ያለበት ደረጃ 1.3 ኪሎ ሜትር የሚሆነዉ የግንባታዉ ቀኝ ክፍል የቁፋሮ እና አፈሩን የማስወገድ ስራ በመከናወን ላይ ነዉ።
ፕሮጀክቱ የሳብ ቤዝ ስራዉን ለማከናወንም ከወዲሁ የሬድ አሽ ግብአት ክምችቱን እያጠናከረ ሲሆን እስካሁን ድረስም 3100 ሜትር ኩብ እንደተሰበሰበ ከፕሮጀክት ሀላፊዉ ከአቶ ገበያዉ መንግስት ማብራሪያ መረዳት ተችሏል።
የፕሮጀክት ሀላፊዉ አያይዘዉም በቅርቡ ለሚጀመረዉ የፕሪካስት ምርት ማምረቻ ቦታም እንደተዘጋጀ እና ለሚመረተዉ ምርትም ግብአት የሚሆን ባለ 02 መጠን ያለዉ ጠጠር እስካሁን 235 ሜትር ኩብ እንዳሰባሰቡ ጎን ለጎንም የፕሮጀክቱ ካምፕ እና ስቶር ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ የስቶር ግንባታ ስራዉም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደ ጀመረ በሳይት ለተገኘዉ የድርጅቱ ማኔጅመንት አስረድተዋል።
ፕሮጀክት ሀላፊዉ በመጨረሻም በሶስተኛ ወገን ችግር ምክንያት አጀማመሩ ቢዘገይም የዋናዉ መ/ቤት ድጋፍ እና የሶስተኛ ወገን ችግር ሙሉ በሙሉ ከተፈታ ግንባታዉን ከተያዘለት ጊዜ በፊት ማጠናቀቅ እንደሚቻል ተናግረዋል።
የምስክ ምልከታ ያደረገዉ የማኔጅመንት ቡድኑም ፕሮጀክቱ በአሁኑ ሰአት ያለበትን ጥሩ ደረጃ አድንቆ በአጠረ ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊዉን ሁል ድጋፍ እንደሚያደርግ ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች አረጋግጧል።