በፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ዳንግላና መራዊ ከተሞች በመገንባት ላይ የሚገኙትን የገጠር የሽግግር ማዕከላት አስፓልት መንገድ ስራ በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡
የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚፈልገውን ጥሬ እቃ ምርት የሚመግቡ አራት የገጠር የሽግግር ማዕከላት (Rural transformation centers) በምርትና ምርታማነታቸው በሚታወቁት በፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ዳንግላና መራዊ ከተሞች በመገንባት ላይ ናቸው። የእነዚህን ፕሮጀክቶች የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ስራ እያከናወነ የሚገኘው ድርጅታችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አራቱንም ፕሮጀክቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የእንጅባራ የገጠር የሽግግር ማዕከል የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት የአስፓልት መንገድ፣ የውሀ ማፋሰሻ እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን የእግረኛ መንገድ ባዞላ ንጣፍና ሌሎች ጥቃቅን ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት ለመጨረስ እየተሰራ ነው፡፡
የፍኖተ ሰላም የገጠር ሽግግር ማዕከል የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ደግሞ በ2013 በጀት ዓመት የተሰጠውን 11,400 ካሬ ሜትር ተጨማሪ የፓርኪንግ ስራ ጨምሮ የመንገድ ስራው ሰብቤዝ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን የቤዝ ኮርስ እና አስፓልት ስራውን ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ግብዓቶች ቀርበዋል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የውሀ ማፋሰሻ ስራው ያለቀ ሲሆን የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ስራውም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
የዳንግላ የገጠር ሽግግር ማዕከል የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ከሶስተኛ ወገን ነፃ በሆነው 735 ሜትር የአስፓልት መንገድ ግንባታው፣ የውሀ ማፋሰሻ እና 49 የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ማንሆሎች ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን የእግረኛ መንገድ ባዞላ ንጣፍና ሌሎች ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፈጸም እየተሰራ ነው።
የመራዊ የገጠር ሽግግር ማዕከል የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከሶስተኛ ወገን በፀዳው ቦታ የውሀ ማፋሰሻ እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ስራው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የመንገድ ስራውም ሰብ ቤዝ ደረጃ ላይ ደርሷል። ቤዝ ኮርስ እና አስፓልቱን ለመስራት የሚያስችል ጠጠርም ተዘጋጅቷል፡፡