ለድርጅታችን ኦፕሬተሮች በጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ገ

ለድርጅታችን የገልባጭ መኪና፣ የውሀ ቦቲ፣ ኬሬር ትራክ እና ሎቤድ ኦፕሬተሮች በጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬ መስከረም 05 2013 ዓ.ም እየተሰጠ ነው። ስልጠናው እየተሰጠ ያለው በድርጅታችን ሎጅስቲክስ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባይሌ እና የመሳሪያዎች አስተዳደርና ጥገና ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ ጌታቸው ደስየ ሲሆን ከጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም እና ስለ አጠቃቀሙ ግንዛቤ ለመፍጠር ትኩረት ያደረገ ነው።

የድርጅታችን ሀብት እያደገ ከመሄዱ ጋር በተያያዘ ዘመናዊ አሰራርን በመከተል የድርጅታችን ሀብት በአግባቡ ማስተዳደር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በድርጅታችን ተሽከርካሪዎች የጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅ እንዲገጠም በስራ አመራር ቦርድ ተወስኖ ተግባራዊ ማደረግ ተጀምሯል ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ አቶ ሞላ ባይሌ ሆኖም ግን ከቴክኖሎጅው ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች መታረም ይኖርባቸዋል ብለዋል። በተለይ ቴክኖሎጅው በተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠመው ለነዳጅ ቁጥጥር ብቻ እንደሆነና ቴክኖሎጅው አክሳሪ እንጅ ጥቅም የሌለው አድርጎ የመቁጠር የተሳሳተ አመለካከት ሊታረም ይገባዋል ተብሏል። በተያያዘም የጂ ፒ ኤስ /GPS/ ቴክኖሎጅው እንዲበላሽ ሆን ብሎ የመስራት አዝማሚያዎች ሊቆሙ ይገባል።

ይህንን ቴክኖሎጅ መጠቀም ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ዘመናዊ አሰራሮችንና ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም የድርጅታችን ንብረት አስተዳደር ውጤታማ ለማድረግ ብሎም የድርጅታችን እድገት በማፋጠን ራዕዩን እንዲያሳካ ለማድረግ መሆኑን ከ ስራ አስኪያጁ ገለፃ መረዳት ተችሏል።