የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

dessie town
የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ከ591 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ መሳይ ሰጣርጌ ገልጸዋል።

ይህን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበረው ፕሮጀክት ኃላፊው ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱን በውለታው ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ቀሪ ግብዓቶችን ለማሟላት በዋና ቢሮና በፕሮጀክት ደረጃ ከፍተኛ ጥረት እየተደገ መሆኑን አስረድተዋል።

በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት በድርጅታችን እየተካሄደ ያለው የክትትልና ድጋፍ ስርዓት የፕሮጀክቱን ችግሮችን እግር በእግር እየፈታ በመሄድ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው ሲሉ ፕሮጀክት ሀላፊው ገልጸዋል።
ነገን እንገነባለን!!!