የኮሬ አዲስ ዓለም አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በፍጥነት ለማጠናቀቅ አስፓልት የማልበስ ስራ መጀመሩ ተገለጸ።

የኮሬ አዲስ ዓለም አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጅክቱ ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ተስፋየ ገልጸዋል። በጥቅሉ 10.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና በገጠርና በከተማ በቅደም ተከተል ከ 7-14 ሜትር ስፋት ያለውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ፕሮጀክት ሃላፊው ከሶስተኛ ወገን ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነው 7 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገዱ ክፍል የቁፋሮና ሙሊት እንዲሁም ሌሎች የስትራክቸር ስራዎች ተጠናቀው አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀምሯል። እስካሁን ባለው አፈፃፀም ከ3 ኪሎ ሜትር በላይ አስፓልት ማልበስ የተቻለ ሲሆን እስከ ሰኔ 30 2013 ዓ.ም ከሶስተኛ ወገን ነፃ የሆነውን አካባቢ ሙሉ በሙሉ አስፓልት ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ፕሮጀክት ሃላፊው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ አቶ ማርከው ሰብስቤ በበኩላቸው የኮሬ አዲስ ዓለም አስፓልት መንገድ ግንባታ ጥራቱን ጠብቆ እየተገነባ መሆኑን ገልፀው አስፈላጊ ድጋፍ ከተደረገለት አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከዚህ በላይ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመገንባት አቅም ያለው ድርጅት ሲሉ ገልጸዋል።