ድርጅቱ ከኮሬ አዲስ አለም የሚደርሰውን 10.74 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ተፈራርሟል። የፊርማ ስነ ስርዓቱ ዛሬ የካቲት 12 2012 ዓ.ም ሲከናወን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅኔር ሀብታሙ ተገኘ፣ ምክትል ዳይሬክተሮች አቶ ሲሳይ በቀለ እና ኢንጂኔር ሂሩት ዮሀንስ፣ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አለማየሁ እና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማው በለጠ ተገኝተዋል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ የሚገኘው እና 10.74 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የኮሬ አዲስ አለም አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በ333,027,799.74 ብር በጀት የሚገነባ ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ይጠናቀቃል።