አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በቡሬ ከተማ ከትንሳኤ ሆቴል እስከ ኢትዮ ቴሌኮም የሚደርስ የ1.52 ኪሎ ሜትር አስፓልት ኮንክሪት መንገድ በ45,639,948.48 ብር ገንብቷል። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጌትነት አጥናፉ እንዳሉት ቀደም ብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ አስፓልት መንገድ ቢሰራም ጥራቱን የጠበቀ ስላልነበር ሊፈርስና ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠር ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን አመኔታ ቀንሶ ቆይቷል። አሁን ግን ይላሉ አቶ ጌትነት አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ጥራቱን አስጠብቆ የገነባው በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፍተኛ እርካታ አግኝቷል።
በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደሩን ገንዘብ የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በሶስት ዓመት ክፍያ ለመስራት በመስማማቱ እንዲሁም ህብረተሰቡን ለማገልገልና ለማገዝ ከምህንድስናው ግምት 24 ሚሊዮን ብር ቀንሶ የአስፓልት መንገዱን የገነባልን በመሆኑ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ሊመሰገን ይገበዋል ሲሉ ከንቲባው አቶ ጌትነት ተናግረዋል። አቶ ጌትነት አክለውም ድርጅቱ በትክክልም የክልላችን ህዝብ እንባ ለማበስ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል በማለት ገልፀዋል።