የወራቤ - ቦጆ በር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክትን በተያዘለት በጀት፣ ጊዜና የጥራት ደረጃ ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ጥሩነህ አዱኛ ገለጹ፡፡

p
የወራቤ - ቦጆ በር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክትን በተያዘለት በጀት፣ ጊዜና የጥራት ደረጃ ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ጥሩነህ አዱኛ ገለጹ፡፡

2.77 ቢሊዮን ብር በሆነ በጀት እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ 41.3 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን በሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ይጠናቀቃል፡፡ እንደ ፕሮጀክት ኃላፊው ገለጻ አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ይህን የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በተያዘለት በጀት፣ ጊዜና የጥራት ደረጃ ለመገንባት በያዝነው በጀት ዓመት በቂ የሰው ሀይል፣ ማሽንና ማቴሪያል መድቦ የተሟሟቀ እንቅስቃሴ እየደረገ ነው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ቢያንስ 50 ከመቶ በላይ የሚሆነውን ስራ ለማጠናቀቅ ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን የገለጹት ፕሮጀክት ኃላፊው ዕቅዱን ለማሳካት አስፈላጊውን የሰው ኃይል፣ ማሽንና ማቴሪያል ያካተቱ የተለያዩ የግንባታ ክሩዎችን በማዋቀር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የተለያዩ የአፈር ስራዎችን የሚሰሩ 03 ክሩዎች እና የስትራክቸር ስራዎችን የሚሰሩ 02 ክሩዎች ተዋቅረው ወደስራ ገብተዋል፡፡ የአስፓልት ጠጠር የማምረት ስራ ለንኡስ ተቋራጭ ተሰጥቶ የፓድ ተከላ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የሞቢላይዜሽን ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለሙሊት የሚሆን ማቴሪያል የማምረት ስራው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ፕሮጀክት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የመንገዱ ባለድርሻ አካላት መንገዱ በፍጥነት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ የበኩላቸውን በጎ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ያሉት ፕሮጀክት ኃላፊው ይህን መልካም አጋጣሚ ከድርጅታችን ጥንካሬ ጋር በማስተሳሰር ፕሮጀክቱን በተያዘለት በጀት፣ ጊዜና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡