በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደብረ ማርያም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ 85 ከመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የደብረ ማርያም መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ማስተማር ስራ እንቅፋት የሚሆን ዘርፈ ብዙ ችግር ካለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው። ትምህርት ቤቱ በክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር የሚገኝ ይሁን እንጅ አንድ ትምህርት ቤት ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን በበቂ ሁኔታ የተሟሉለት አልነበረም፡፡ የመማሪያ ክፍሎች ከመጎዳታቸውም በላይ ለህጻናቱም ሆነ ለመምህራን አስጊ መሆን፣ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር አለመሟላት፣ የመፀዳጃ ቤት አለመኖር፣ የስፖርት ሜዳ ምቹ አለመሆን ትምህርት ቤቱ ከነበሩበት ችግሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ማህበራዊ ሀላፊነቱን የማይዘነጋው አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅትም የደብረ ማርያም ትምህርት ቤት ድጋፍ የሚያስፈልገው መሆኑን በመረዳት ሙሉ ወጪውን በራሱ ሸፍኖ አምስት ክፍሎች ያሉት አንድ የመማሪያ ብሎክ ፣ የር/መ/ር ቢሮ፣ ስቶር እና የመምህራን ማረፊያ ክፍሎች፣ የወንዶችና የሴቶች መምህራንና ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት እንዲሁም የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ማሟላት እና ግቢውን በግሬደር የማስተካከል ስራ ለመስራት ቃል በገባው መሰረት ግንባታውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአሁኑ ሰዓት ከ85 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፊኒሽግ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማዋል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡