«በ2017 በጀት ዓመት ካለፈው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አቅደን እየሰራን ነው» አቶ መብት አድማስ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ
በ2017 በጀት ዓመት ካለፈው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አቅደን እየሰራን ነው ሲሉ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ ገለጹ። ዋና ስራ አስኪያጁ ይህን ያሉት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት የስራ እንቅስቃሴን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ለብዙሐን መገናኛ ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት በ2016 በጀት ዓመት ችግር ፈች የሆኑ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ጥሩ አፈጻጸም ማስመዝገብ ችሏል። በተለይ እንደ ተከዜ ድልድይ ያሉ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበሩ ፕሮጀክቶችን ምሽትን ጨምሮ በመስራት ከታቀደው ጊዜ ቀድሞ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡ እንዲገለገልበት ማስቻሉ ድርጅቱ በደንበኞቹ ዘንድ እውቅና እንዲሰጠው አድርጓል። እንደ ክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግንባታ ስራ ፈታኝ የሆኑ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ችግሮችን ተቋቁመን መስራት በመቻላችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ237 ሚሊዮን በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
እንደ ድርጅት በያዝነው በጀት ዓመትም ከ5.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ለመስራት አቅደን ወደ ስራ ገብተናል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ዕቅዳችንን ለማሳካት ጊዜ ያለውን ፋይዳ ከተሞክሯችን ስለተረዳን በቀን ብቻ ሳይሆን ምሽትን ጨምሮ እየሰራን እንገኛለን። በተለይ በባህር ዳር ከተማ እየገነባነው የምንገኘውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ በአሁን ጊዜ እስከ ምሽት ስድስት ሰዓት እየሰራን ሲሆን በቀጣይም በሶስት ፈረቃ በማድረግ ሙሉ 24 ሰዓት በስራ ላይ የምናሳልፍ ይሆናል። ምሽትን ጨምሮ የመስራት የስራ ባህል ማዳበራችን ድርጅታችንም ትርፋማ ያደርጋል፤ ህብረተሰቡም ቶሎ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል ያሉት አቶ መብት አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በግንባታ ጥራት እንደማይደራደረው ሁሉ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት መጨረስ የስራ ባህሉ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።