የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞች በህልውና ማስከበር ዘመቻው ለተሰማራው ጀግናው ሰራዊታችን የሚያደርጉትን የስንቅ ዝግጅት አጠናክረው ቀጥለዋል።
ኢትዮጵያን ማፍረስ በተለይም አማራን ማጥፋት ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው የትግራይ ወራሪ ሀይል እያደረሰው የሚገኘውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ለመከላከል ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉና አንጸባራቂ ድልም እየተጎናጸፉ ይገኛል።
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አመራሮች እና ሰራተኞችም ጦር ግምባር ለተሰማራው ጀግናው ሰራዊታችን ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን በማረጋገጥ ላይ ናቸው። በትናትናው ዕለት ሁለተኛ ዙር የስንቅ ዝግጅት የተጀመረ ሲሆን በአጠቃላይ 100 ኩንታል በሶ አዘጋጅቶ ለመለክ ታቅዷል። በመጀመሪያው ዙር 15 ኩንታል በሶ ተዘጋጅቶ መላኩ የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም የድርጅታችን አመራሮች እና ሰራተኞች በቀጣይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
የመንግስታችን የክተት ጥሪ ተቀብለው በተለያዩ ግምባሮች ተሰማርተው የሚገኙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እብሪተኛውን ቡድን ላይ በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የሀገራችንን ሰላም እና ደህንነት እንደሚያረጋግጡ አያጠራጥርም።