''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ለድርጅታችን የዋና ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

eda
''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ለድርጅታችን የዋና ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግሥት ሠራተኛው ሚና በሚሉ ሁለት ዓበይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከየካቲት 04-05/ 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል። በስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ከተካሄደ በኋላ በድርጅታችን አመራሮች በኩል ማጠቃለያ ሀሳብ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።
eda