የድርጅታችን የዋና ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ እየገነባቸው የሚገኙ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

crusher
የድርጅታችን የዋና ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ እየገነባቸው የሚገኙ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

የድርጅታችን የዋና ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ እየገነባቸው የሚገኙ የዋርካው- ዘንዘልማ፣ የቅዱስ ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ እና የመብራት ሀይል- ማርዳ- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የየፕሮጀክቶቹ ኃላፊዎች ተገኝተው ስለ ፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ የፊዚካል ስራ እንቅስቃሴ ገለጻ የሰጡ ሲሆን ከተሰጠው ገለጻ በመነሳት ጎብኝዎች የፕሮጀክቶቹኝን ዋና ዋና የፊዚዘካል ስራዎች ተዘዋውረው ምልከታ አካሂደዋል፡፡

የዋርካው- ዘንዘልማ እና የቅዱስ ገብርኤል- አዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ እንደገለጹት የዋርካው- ዘንዘልማ ፕሮጀክት አጠቃላይ የአፈር ስራው ተጠናቆ አስፓልት የለበሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የእግረኛ መንገድ እና የኤሌክትሪካል ስራው እየተከናወነ ነው፡፡ ከቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን- አዲሱ አስፓልት ያለው መንገድ ከሶስተኛ ወገን ነጻ የሆነው የመንገዱ ክፍል የአፈር ስራው በመጠናቀቅ ላይ ያለ ሲሆን ከአዲሱ አስፓልት- ምድረገነት ታክሲ ማዞሪያ ያለው ደግሞ የመጀመሪያ ሌየር አስፓልት ስራ ተጠናቋል፡፡

የመብራት ሀይል- ማርዳ- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ አባይነህ ደሳለኝ በበኩላቸው ከሶስተኛ ወገን ነጻ በሆነው የመንገዱ ክፍል በሙሉ የቆረጣ እና ሙሊት ስራ እየተከናወነ እንደሆነና የስትራክቸው ስራዎችም በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አውስተዋል፡፡

የዋናው ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች በአካል ተገኝተው ፕሮጀክቶቹን መጎብኘታቸው ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እንደሚያስችላቸው ይጠበቃል፡፡

ስለ ድርጅታችን መረጃ ለማግኘት፡-
ፌስ ቡክ፡ www.facebook.com/AmharaRoadWorksEnterprise
ድረ ገጽ፡ www.arwe.et
ቴሌግራም፡ www.t.me/AmharaRoadWorksEnterprise
ዩቲዩብ፡ www.youtube.com/AmharaRoadWorksEnterprise ይጎብኙ፡፡
crusher