«ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል!» በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀን በድርጅታችን ተከበረ።

corruption
«ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል!» በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀን በድርጅታችን ተከበረ።

የፀረ ሙስና ቀን በየዓመቱ በህዳር ወር መጨረሻ ይከበራል። በሀገራችንም ሆነ በክልላችን በዘንድሮው ዓመት ለ19 ጊዜ የፀረ ሙስና ቀን እየተከበረ ነው። በድርጅታችንም ዛሬ ህዳር 24 2016 ዓ.ም «ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል» በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከብሮ ውሏል። ለውይይት መነሻ የሚሆን የመወያያ ሀሳብ በድርጅታችን የፕላንና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ደጋፊ ስራ ሂደት መሪ አቶ ተገኘ ወርቁ የቀረበ ሲሆን የድርጅታችን ሎጅስቲክስ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ጋሻው አስማሜ ደግሞ ውይይቱን መርተውታል።

በውይይቱ ሙስና ዘርፈ ብዙና የተወሳሰበ፣ አፈጻጸሙም እየረቀቀና እየሰፋ በመምጣቱ በአሁኑ ሰዓት የመልካም አስተዳደር ችግር እና የልማት ጸር ከመሆን አልፎ የሀገር ህልውናን እየፈተነ እንደሚገኝ ተነስቷል። ሙስናን ለመከላከል በሀገር ደረጃም ሆነ እንደ ክልል ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም የሚፈለገው ውጤት ሊመዘገብ አልቻለም። በመሆኑም ሙስናን መከላከል የጸረ-ሙስና ወይም የአንድ አካል ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመሆኑ ሁሉም ቃል ኪዳን ከመግባት ባለፈ በተግባር የየድርሻቸውን መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።