የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ድርጅታችን በባህር ዳር ከተማ ውስጥ የሚገነባው የመብራት ሃይል- ማርዳ ቀለም- ኤርፖርት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ አባይነህ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡
የሚገነባው መንገድ 8.5 ኪ.ሜ ርዝመት እና 40 ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ የሆነ የመኪና፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድን እንዲሁም አረንጓዴ ቦታን ያካተተ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከሶስተኛ ወገን ችግር ነጻ በሆነው የመንገዱ ክፍል የቆረጣና ሙሊት ስራዎች አፈጻጸም ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በተያያዘም በፕሮጀክቱ ለተደራጁ 11 ማህበራት የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የዲች ግንባታ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በፕሮጀክቱ ለድጋፍና ክትትል የተገኘው ቡድን አባላት በበኩላቸው የፕሮጀክቱ አመራር እና የሰራተኛው ትጋት በጣም ጥሩና የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት በዋና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በኩል እየተካሄደ ያለው የክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ፈጣን የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት የፕሮጀክቱን ችግሮች እግር በእግር እየፈታ በመሄድ አሁን ላለው የተሻለ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ሲሉ ፕሮጀክት ሀላፊው ገልጸዋል።