የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ከ591 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት በድርጅታችን እየተገነባ የሚገኘው የደሴ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ መሳይ ሰጣርጌ ገልጸዋል።
ይህን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበረው ፕሮጀክት ኃላፊው ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱን በውለታው ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ቀሪ ግብዓቶችን ለማሟላት በዋና ቢሮና በፕሮጀክት ደረጃ ከፍተኛ ጥረት እየተደገ መሆኑን አስረድተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት 4 መንገዶች ማለትም ከወሎ ሆቴል- ደሴ ከተማ አገልግሎት፣ ከመላኩ ደሳለኝ ሆቴል- ደሴ ሆስፒታል፣ ከኮሽምበር- ገራዶ እና ከመናፈሻ- ተቋም አስፖልት ለማልበስ ታቅዶ እስካሁን 2ቱ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ የመጀመሪያውን የአስፖልት ላየር የለበሱ ሲሆን ቀሪወቹንም እስከ ሰኔ 30 2015 ዓ.ም ድረስ አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ መሆኑን ፕሮጀክት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት በድርጅታችን እየተካሄደ ያለው የክትትልና ድጋፍ ስርዓት የፕሮጀክቱን ችግሮችን እግር በእግር እየፈታ በመሄድ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው ሲሉ ፕሮጀክት ሀላፊው ገልጸዋል።
ነገን እንገነባለን!!!