የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የ2014 በጀት ዓመት የፕሮጀክቶች የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
በግምገማው የሁሉም ኘሮጀክቶች የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በኮንስትራክሽን ዋና የሥራ ሂደት በኩል ቀርቦ ግምገማ አዘል ውይይት ተደርጐበታል፡፡
በመድረኩም የድርጅቱ ኮር አመራር፣ የማኔጅመንት አባላት የኘሮጀክት ኃላፊዎች እና ኦፊሰ መሃንዲሶች፣ የዋናው ቢሮ የኮንስትራክሽንና ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱም በተጠናቀቀው ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና መስተካከል ያለባቸው እጥረቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተካሂዶ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ላይ መግባባት ተደርሷል፡፡
በመጨረሻም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስማማው ዓለማየሁ በፕሮጀክቶች ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ያጋጠሙ ውስጣዊና ውጫዊ የሆኑ ዋና ዋና ችግሮችን በጋራ በመፍታት በቀጣይ ቀሪ ወራት የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተቀይሮ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡