አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ወደ ኮርፖሬሽንነት ደረጃ ማደጉን ተከትሎ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችለውን አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት አጸደቀ። 
ድርጅቱ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ ማደጉን ተከትሎ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችል አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት መፅደቁን ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ ከጊዜ ጊዜ ካፒታሉን እና የመፈጸም አቅሙን ይበልጥ እያሳደገ በመምጣቱ እና በአሁኑ ሰዓት የያዛቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጨምሮ ወደ ፊት የሚይዛቸውን ሰፋፊ የልማት ስራዎች በብቃት ለማከናወን እንዲችል ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ የኮርፖሬሽንነት ደረጃ እንዲያገኝ የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 214/2016 የወሰነ መሆኑ ይታወሳል።
ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በአስፓልት መንገድ እና ድልድይ ግንባታ ስፔሻላይዝ በማድረግ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመገንባት ኃላፊነት ወስዶ በጥራት እያከናወነ ይገኛል። በአጭር ጊዜ አሰራሩን በማሻሻል ትልልቅ የአስፓልት መንገዶችን እና ድልድዮችን በጥራት እና በፍጥነት ገንብቶ ማስረከብ የሚያስችል አቅም መፍጠር የቻለው ኮርፖሬሽኑ በመደበኛ የሥራ ሰዓት ብቻ እየሰሩ በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየት እንደማይቻል ተገንዝቦ በሶስት ፈረቃ በመስራት ፕሮጀክቶችን ከውለታ ጊዜያቸው ቀድሞ የማጠናቀቅ በጎ ጅምር እያዳበረ መጥቷል።
ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት በድምሩ 11 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ፕሮጀክቶችን የግንባታ ውል ወስዶ እየፈጸመ ሲሆን በዓመት ከ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ስራ መስራት የሚችልበትን አቅም ፈጥሯል። የመፈጸም አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በደንበኞቹ ዘንድ እምነትን ያተረፈው ኮርፖሬሽኑ ይህንን የመፈፀም አቅሙን ይበልጥ በማሳደግ ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል የሚያስችል የመዋቅር ጥናትን ሲያስጠና ቆይቷል። መዋቅራዊ አደረጃጀት የተቋማትን የወደፊት የስራ አፈጻጸም ጭምር የሚወስን በመሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ መስራት ስለሚያስፈልግ ጥናቱን ሳይንሳዊ ከማድረግ ባለፈ ከነባራዊ እውነታው ጋር የሚስማማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። የስራ አመራር ቦርዱ የመዋቅሩ ጥናት መነሻ ሁኔታዎችን ፣ በጥናቱ የተመለሱ መዋቅራዊ ችግሮችን እና አዲሱ አደረጃጀት ለኮርፖሬሽኑ ቀጣይ ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት ያለዉን ፋይዳ በጥልቀት ከገመገመ በኋላ መዋቅሩ በይዘት ደረጃ ሊያካትታቸውና ሊያስተካክላቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዲስተካከሉ አቅጣጫ በመስጠት የቀረበውን የመዋቅር ጥናት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
ተቋሙ ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ ከፍ ማለቱን ተከትሎ የተሰራው አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት ወደ ትግበራ እንዲገባ የተፈቀደ በመሆኑ ለመላው የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ክቡር ቦርድ ሰብሳቢው አቶ ኃይሌ አበበ ይህንን የለውጥ ሂደት እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም ለላቀ ውጤት መዘጋጀት እንደሚገባ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።