አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የ2.777 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ተፈራረመ።
ድርጅታችን የወራቤ ቦዦበር አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን 2,777,252,904.36 ብር በሆነ በጀት ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር ተፈራርሟል።
የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱ የፊርማ ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እና የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ መካከል ተከናውኗል።
የመንገድ ግንባታው በሁለት ዓመት የኮንትራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወራቤ ቦዦበር አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት 41.3 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው ሲሆን በከተማ 21.5ሜ፣ በቀበሌ 12ሜ እና በገጠር ደግሞ 10 ሜ ስፋት ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ አነስተኛ እና ከፍተኛ ፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦዎች እና ከልቨርቶች ሥራ ያካትታል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ የድርጅታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መብት አድማስ ግንባታውን በኮንትራት ጊዜው ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ በማከናወን ለማስረከብ ድርጅታችን ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጅ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ በጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ከድርጅታችን አመራርና ሰራተኞች ባለፈ የግንባታው ባለቤት እና የአካባቢው ማህበረሰብን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህን በውል ተገንዝበው የድርሻቸውን ሁሉ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ነገን እንገነባለን !!