የዋርካው ምድረ-ገነት ዘንዘልማ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገለጹ።

የዋርካው ምድረ-ገነት ዘንዘልማ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገለጹ።

በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የዋርካው ምድረ-ገነት ዘንዘልማ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን በፍጥነትና በጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ተስፋለም አድባሩ ገልጸዋል፡፡ የ3.2 ኪ. ሜትር ርዝማኔ እና 30 ሜትር ስፋት ያለው ይህ የአስፓልት መንገድ ግንባታ የአፈር ቁፋሮ እና ሙሊት ስራው ሙሉ በመሉ ተጠናቆ ሰብቤዝ ደረጃ የደረሰ ሲሆን የመጀመሪያ ሌየር (ባይንደር ኮርስ) አስፓልት የማልበስ ስራውም ተጀምሯል። የውሀ ማፋሰሻ ስራዎችም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን የእግረኛ መንገድ እና አረንጓዴ ስፍራ ስራዎችም ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆኑን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ችለናል።

በአጠቃላይ ይህን የአስፓልት መንገድ ግንባታ እስከ ሰኔ 30 2015 ዓ.ም ፍጥነትና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ፕሮጀክት ሀላፊው ቢትመንና ጠጠርን ጨምሮ ለአስፓልት ስራ የሚያገለግሉ ዋና ዋና ግብዓቶች አቅርቦት ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲሱ አስፓልት ምድረ-ገነት አስፓልት መንገድ የቆረጣና ሙሊት ስራው ተጠናቆ ለአስፓልት ዝግጁ ሲሆን የአስፓልት ስራውን በቅርቡ ለመስራት ታቅዷል። በተመሳሳይ ከቅ/ገብርኤል- ቅ/ኪዳነ ምህረት- አዲሱ አስፓልት ያለው መንገድም የቆረጣ እና ሙሊት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ፕሮጀክት ኃላፊው አቶ ተስፋለም አድባሩ ገልጸዋል።