Denbecha- Feres bet- Seqela and Bibugn link Road Asphalt Project performance

ready for Asphalt
የደንበጫ- ፈረስ ቤት- ሰቀላ እና ቢቡኝ አገናኝ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስፓልት የማንጠፍ ስራ ለመጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

እየተጠናቀቀ በሚገኘው በጀት ዓመት በፕሮጀክቱ የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን አስፓልት የማንጠፍ ስራ ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡
በፕሮጀክቱ የቆረጣና ሙሊት ስራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነው መንገድ ለአስፓልት ስራ ዝግጁ ነው ተብሏል፡፡ ለአስፓልት ስራ ከሚያስፈልጉ ዋና ዋና ግብዓቶች አንጻር የቢትመን ግዥ ተፈጽሞ በመጓጓዝ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአስፓልት ጠጠር በበቂ ሁኔታ ማቅረብ የሚችሉ 02 የኪራይ እና 01 የራስ ሀይል ክሬሸሮች /የድንጋይ ወፍጮዎች/ ጠጠር በመፍጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም 02 አስፓልት ማምረቻ የአስፓልት ፕላንቶች ዝግጁ መሆናቸው ተገልጧል፡፡
Crushed material