ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የአደረጃጀት፣ የስያሜ እና የሎጎ ለውጥ ይፋዊ የማስተዋወቂያ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የኮርፖሬሽኑ መሪዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የቀድሞው የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የአሁኑ ኅብር የኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሲመሠረት የነበረውን የኮንስትራክሽን ጉድለት በመሙላት የመሠረተ ልማት ዘርፍን በማጠናከር የመንገድ ተደራሽነትን ለማሳደግ ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ያሉት ቦርድ ሰብሳቢው ፈተናዎችንም አልፏል ብለዋል። ሌሎች ያልደፈሩትን መልክዓ ምድሮችን ደፍሮ በመግባት እና በመሥራት ለሕዝብ እና ለልማት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየቱንም ገልጸዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሠራው መሠረተ ልማትም ገጠርን ከከተማ በማገናኘት መንግሥታዊ አገልግሎትን ለሕዝቡ ማድረስ እንደቻለ ገልጸዋል። ክልሉ ከዓመት ዓመት ላስመዘገባቸው ዕድገቶች ትልቅ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል። ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከ3 ሺህ በላይ ሠራተኞችን ይዞ ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ ማደጉን እና በ2030 ዓ.ም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከአፍሪካ ተመራጭ የግንባታ ተቋራጭ ለመኾን ራዕይ አስቀምጦ እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።