«አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለሌሎች ድርጅቶች ምሳሌ መሆን እንደሚቻል ያስተማረ ድርጅት ነው !» ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የአመሥድ ቦርድ ሰብሳቢ
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ለሌሎች ድርጅቶች ምሳሌ መሆን እንደሚቻል ያስተማረ ድርጅት ነው ሲሉ የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የአመሥድ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ ገልጸዋል። ድርጅቱ በአንድ ወቅት አፈጻጸሙ ቀንሶ የነበረ ቢሆንም የነበሩ ችግሮችን ሁሉ ፈቶ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉ ጫናዎችን ሁሉ ተቋቁሞ ባለፉት ዓመታት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገበ ሲሆን በተያየዘው በጀት ዓመትም የያዛቸውን ፕሮጀክቶች በተሻለ ፍጥነት እና ጥራት እየገነባ ይገኛል።
ድርጅቱ ቀድሞ ይታወቅበት ከነበረው ፕሮጀክቶችን በጥራት የመገንባት መልካም ልምድ በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት ከተለመደው የጊዜ አጠቃቀም ወጥቶ በሶስት ፈረቃ በመስራት ፕሮጀክቶችን ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድሞ የማጠናቀቅ ጥሩ ጅምር እያዳበረ መጥቷል። በዚህም ከውድቀት በመነሳት ምሳሌ መሆን እንደሚቻል ያስተማረ ብቻ ሳይሆን በመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ካምፓኒዎች ዘንድ እምነት የሚጣልበት ድርጅት መሆን ችሏል ሲሉ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ ገልጸዋል።