በጋሸና፤ ላሊበላ ፤ብልባላ ፤ሰቆጣ ሎት 01 አስፖልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም እና የ2018 የዕቅድ ትውውቅ ተካሄደ።

m
የኮርፓሬሽኑ ዲዛይን ዝግጅት እና ውል አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራራ ገረመው የ2017 ዓ.ም አፈፃፀምን እና የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለፕሮጀክቱ አመራርና ሰራተኞች አቅርበዋል። በውይይት መድረኩ በዋና ሥራ አስፈፃሚ ማዕረግ የዋና ሥራ አስፈፃሚ አማካሪ ኮለኔል አለበል እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

የፕሮጀክት ሰራተኞችም በ2017 ዓ.ም የኮርፖሬሽኑ አፈፃፀም ከዋናው ቢሮ እስከ ፕሮጀክት ያለው የመላው አመራርና ሰራተኛ የድካም ውጤት መሆኑን በመግለፅ ለ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ራሳችንን ማዘጋጀት ይጠበቅብናል ብለዋል። ሰራተኞችም በውይይቱ ኮርፖሬሽኑ የፕሮጀክቱን የሥራ ስሜት ተነሳሽነትን በቅርበት በመከታተል ለፕሮጀክቱ ጊዜ የማይሰጡ ወሳኝ የሆኑ ግብዓቶች ተለይው እንዲቀርቡላቸው እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ጠንካራና ውጤታማ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፈልገው መሆኑንን ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ያለበት ከመሆኑ የተነሳ የግንባታ ሂደቱን በተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ከፕሮጀክቱ አመራርና ሰራተኞች የስራ መነሳሳትን ለመጠቀም የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ያልተገደበ ወቅታዊ ፈጣን ውሳኔ እንዳይለየን በማለት ተናግረዋል።
በመጨረሻም ኮለኔል አለበል አማረ በፕሮጀክት አመራርና ሰራተኞች ፕሮጀክቱን በዕቅዱ መሰረት ለመፈፀም እንዲቻል በስጋት የቀረቡ የግብዓት አቅርቦት እና የቅርብ ክትትልና ድጋፍን ኮርፖሬሽኑ አቅም በፈቀደ መልኩ የትኩረት ማዕከል አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ በሁሉም ፕሮጀክቶቻችን በምክንያት ታጥሮ የማይቆም ችግር ፈች የፕሮጀክት አመራርና ሰራተኛ ሆኖ መገኘት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በመጨረሻም የፕሮጀክቱ አመራርና ሰራተኞች ባለ 8 ነጥብ አቋም መግለጫ አስምተው ውይይቱን አጠናቀዋል።
n