በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከወራቤ ቦዥበር እየተገነባ የሚገኘውን አስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክትን በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችል በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወነ ነው። ኢንጅነር መብት አድማስ የኅብር ኮንስትራክሽ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ ስፈፃሚ።

photo of Mr. Mebit
የፕሮጀክቱን አስፖልት መንገድ ሥራን በወቅቱ ለማንጠፍ በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከተሟሉ ዋና ዋና ግብዓቶች ውስጥ አዳዲስ ዘመናዊ አስፖልት ፕላንት፣ ዘመናዊ ክሬሸር ፣ አስፓልት ፔቨር እና ሌሎች ለመንገድ ግንባታው ወሰኝ የሆኑ ግብዓቶች ተሟልተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ቢትመን፣ የአስፓል ንጣፍ የሚውሉ የተለያዩ የጠጠር ምርቶች ፣የማጠናከሪያ ብረትና የሲሚንቶ ግብዓቶች ሁሉ ዝግጁ ሆነዋል።

ይህንንም የዝግጅት ምዕራፍ በምልከታ ያረጋገጡት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኒ ቢልካ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሴትራል ሪጅን ዳይሬክተር ኢንጅነር ደጀኔ ጉቱ፣ የአማካሪ ደርጅቱ SG ባለቤት አቶ አዳነ ባደለው እና የፕሮጀክቱ አመራሮች ናቸው።

በጉብኝቱ ስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ፕሮጀክቱን በ2018 ዓ.ም ካሳለፍናቸው ዓመታት በተሻለ መንገድ ለመፈፀም ኮርፖሬሽኑ የሄደበትን ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራን አመስግነዋል። የዞን ከስተዳደሩም ለፕሮጀክቱ አስፋልት የማንጠፍ ስራ የሚያሳልጡ ሁለንተናዊ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የኮርፓሬሽኑ ዋና ስራ አሥፈፃሚ ኢንጅነር መብት አድማስ የዞን አስተዳደሩ ለአስፓልት መንገድ ግንባታ ሥራው ስኬት ከጎናችን ለመቆም ያሳዩትን ቁርጠኛ አመራርን አድንቀዋል።

ኮርፖሬሽኑም እንደ ኮንትራክተር ለወራቤ ቦጆበር አስፓልት ማንጠፍ ስራው ፈታኝ የሆኑ በቀላሉ ገብያ ላይ የማይገኙ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ግብዓቶችን በከፍተኛ ጥረት እና ወጭ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ችለናል ብለዋል።

በመጨረሻም ዋና ሥራ አሰፈፃሚው የዞኑ አስተዳደር በስራ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን እግር በእግር በመፍታት ከጎናችን እስከቆመ ድረስ ኮርፖሬሽኑ በሁለት ሽፍት የመስራት የስራ ባህሉን ተጠቅሞ የመንገድ ግንባታውን በያዝነው በጀት ዓመት አጠናቀን እናስረክባለን ብለዋል።