በኮርፖሬሽኑ የERP ሶፍት ዌር ትግበራ ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ ERP ሶፍት ዌር ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢራራ ገረመው አስታውቀዋል፡፡ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሚገነባቸውን ፕሮጀክቶች እና አጠቃላይ ሀብቱን በአግባቡ ለማስተዳደርና ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን አሰራሩን ለማዘመን የሚያስችለውን ERP ሶፍት ዌር ከ ERP Solutions Ethiopia plc ጋር በመተባበር ሲያስለማ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ሶፍትዌሩ የማልማት ስራው በአብዛኛው በመጠናቀቁ ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን የገለጹት የቴክኒካል ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ቢራራ በአሁኑ ሰዓት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ERP የአንድን ተቋም የተለያዩ ሐብቶች በተቀናጀ፣ ወጭ ቆጣቢ በሆነ እና ብክነትን በሚቀንስ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ሶፍት ዌር እንደሆነ የገለጹት የኮሚቴው ሰብሳቢ ኮርፖሬሽኑ ከስራ ባህሪው አንጻር ከፍተኛ ሐብት የሚያንቀሳቅስ እና ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ተቋሙ ሀብቱን በአግባቡ ለማስተዳደርና አሰራሩን በማዘመን ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የERP ሶፍት ዌር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ አብራርተዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ለቴክኖሎጅ እንግዳ ባይሆንም ይጠቀምባቸው የነበሩ ሲስተሞች ግን የተቀናጁ አልነበሩም ያሉት አቶ ቢራራ አሁን የለማው ERP ሲስተም ግን በስሩ የኮንስትራክሽን ኦፐሬሽን፣ ኮንትራት አስተዳደር፣ ፋይናንስ፣ ግዥና አቅርቦት፣ ንብረት፣ የሰው ሀይል አስተዳደር፣ የመሳሪያ አስተዳደር፣ የማርኬቲንግ፣ እንዲሁም የጠቅላላ ሪፖርትን ያቀፈ ትክክለኛ መረጃን ከአንድ ቋት ለማግኘት የሚያስችል እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ቢራራ በገለጻቸው ሶፍትዌሩን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር በቅድሚያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አስፈላጊ በመሆናቸው የአሰልጣኞች ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡ የአሰልጣኞች ስልጠናን የወሰዱት ሰልጣኞች በቀጣይ በፕሮጀክቶች ላሉ ሰራኞች ሶፍትዌሩን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ስልጠና እንደሚሰጡም አቶ ቢራራ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የዋና ቢሮ ሰራተኞች በተለያዩ ምድቦች ተከፍለው ስልጠናውን እየወሰዱ ሲሆን በቀጣይ የማኔጅመንት አባላት ስልጠና ከተሰጠ እና የፕሮጀክት ሰራተኞችም ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ሶፍትዌሩን በጥቅምት ወር ሙሉ በሙሉ መተግበር እንደሚጀመር አቶ ቢራራ አስታውቀዋል፡፡ በተያያዘም ሶፍትዌሩን ያበለጸገው ድርጅት ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅበት እና ወደፊት በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት ድጋፍ ማድረግ እንደሚቀጥል የኮሚቴው ሰብሳቢ ገልጸዋል፡፡