ትልልቅ የመንገድ፣ ድልድይ እና ሌሎች መሰረተ-ልማት አውታሮችን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ኮርፖሬሽኑ አሰራሩን አውቶሜት በማድረግ ይበልጥ ለማዘመንና ውጤታማ ለመሆን የሚያስችለውን ERP ሶፍት ዌር እያስለማ ይገኛል፡፡ ከስራ ባህሪው አንጻር ከፍተኛ ሐብት የሚያንቀሳቅስ እና የሚጠቀም በመሆኑ እንዲሁም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ የተሳለጠ እና ዘመናዊ አሰራር እንዲሁም ሐብት አስተዳደር እንደሚያስፈልገው እሙን ነው። ይህንንም ተግባር ለመከወን ከፍተኛ በጀት በመመደብ Enterprise Resource Planning /ERP/ የተሰኘ የተቀናጀ ሶፍት ዌር በዘርፉ ብዙ ልምድ ካለው ERP Solutions Ethiopia plc ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር እያስለማ ይገኛል።
ERP ምንድን ነው? ለተቋሙ የሚያሰገኘው መሰረታዊ ጥቅሙስ? የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲመልሱልን የጠቅናቸው የኮርፖሬሽኑ ERP ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢራራ ገረመው ERP የአንድን ተቋም የተለያዩ ሐብቶች በተቀናጀ፣ ወጭ ቆጣቢ በሆነ እና ብክነትን በሚቀንስ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ሶፍት ዌር እንደሆነ ገልጸዋል። ኮርፖሬሽናችን ከዚህ ቀደም ለቴክኖሎጅ እንግዳ ነበር ባይባልም የፋይናንስ፣ የሰው ኃይል እና የማቴሪያል ሐብቶቹን ለማስተዳደር ይጠቀምባቸው የነበሩ ሲስተሞች ግን የተቀናጁ አልነበሩም። አሁን እያስለማው የሚገኘው ERP ሲስተም ግን በስሩ 06 ሞጁሎችን ማለትም የኮንስትራክሽን ኦፐሬሽን፣ ኮንትራት አስተዳደር፣ ፋይናንስ፣ ግዥና አቅርቦት፣ ንብረት እንዲሁም የሰው ሀይል አስተዳደርን ያቀፈ ትክክለኛ መረጃን ከአንድ ቋት ለማግኘት የሚያስችልና በፊት የነበሩ ክፍተቶችን ሁሉ የሚሞላ ነው ሲሉ አቶ ቢራራ ተናግረዋል። ስለዚህ በጥቅሉ ካየነው ተቋሙ ያሉትን ሐብቶች በትክክል ለመለየት፣ ለማወቅና በአግባቡ ለመጠቀም እንዲሁም በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር በመልማት ላይ የሚገኘው ሶፍት ዌር ጉልህ ፋይዳ አለው ሲሉ አብራርተዋል።
በተጨማሪም እንደ ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢው ገለጻ ሲስተሙ ትልቅ ፋይዳ ያለው እንደመሆኑ መጠን በአመራሩ ዘንድ ከፍተኛ ተሳትፎ እና ትኩረት አግኝቶ እየተሰራበት ይገኛል። ሲስተሙ ከበለጸገ በኋላ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ማቴሪያሎችን ለማሟላት እንዲሁም ፈጻሚው አካል ትክክለኛ ግንዛቤ ይዞ ወዶት እንዲተገብረው የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ አቶ ቢራራ ገረመው አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ሶፍት ዌሩ ለተጠቃሚዎች ምን ያህል ቀላል ነው? ስንል የጠየቅናቸው ERP Solutions Ethiopia plc ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅረማርያም ተሾመ ሲስተሙ ከጅምሩ ዲዛይን ሲደረግ ለተጠቃሚዎች ቀላል እንዲሆን፣ የኮርፖሬሽኑን ብራንድ ቀለማት እንዲይዝ፣ የተጠቃሚዎችን የዓይን ጤና ተስማሚ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ ስለሆነ ለአጠቃቀም በጣም ቀላል ነው ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም ተጠቃሚዎች ስራቸውን ለመስራት ሶፍት ዌሩን እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከሚሰጣቸው የተግባር ስልጠናዎች በተጨማሪ ሶፍት ዌሩ ላይ በጽሁፍ እና በቪዲዮ የተዘጋጁ ጋይዶች የተካተቱ በመሆኑ በስራ ወቅት ሊገጥማቸው ለሚችል የግንዛቤ ችግሮች በራሳቸው በቀላሉ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ ሲሉ አብራርተዋል።