ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር "ግብር ለሀገር ክብር" በሚል መሪ መልዕክት ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና መስጠት እና የታክስ ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። በእውቅና እና ንቅናቄ መድረኩ የአብክመ ርእሰ መሥተዳደር የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ግብርን በአግባቡ ማሥተዳደር በክልሉ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ የገለጹት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ነጻ ለመውጣት፣ የኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ እና የተረጋጋ ሀገር ለመፍጠር ገቢን ማሳደግ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በቅንነት እና በታማኝነት ግብር ለከፈሉ ግብር ከፋዮችም ምስጋና አቅርበዋል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽንም ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር በቅንነትና በታማኝነት በመክፈሉ ከፍተኛ የሆነውን የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማት ማግኘት ችሏል።